Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Zayse translations by topic.
ሰላምታ መስጠት::
ጤና ይስጥልኝ፣ እንደምን አሉ?
ደህና፣ ፈጣሪ ይመስገን፡፡
ደህና ነኝ፣ አመሰግናለሁ፡፡ አንተስ/ቺስ?
ታድያስ! ስላገኘሁህ/ሽ ደስ ብሎኛል፡፡
እንደምን አደርክ/ሽ?/ እንደምን ዋልክ/ሽ? እንደምን አመሸህ/ሽ?
መሰናበት
ደህና ሁን/ኚ!
ደህና ሁን/ኚ /ቻው!
አትጥፋ/ፊ፡፡
ራስህን/ሺን ጠብቅ/ቂ፡፡
ነገ እንገናኝ፡፡
ደህና እደር/ሪ፡፡
የበዓላት ጊዜ መልካም ምኞት
መልካም ገና! ለሁላችን፡፡
መልካም አዲስ ዓመት! ለሁላችን፡፡
መልካም በዓል፡፡ ለሁላችን፡፡
የልደት ቀን መልካም ምኞት
መልካም ልደት! አመሰግናለሁ፡፡
መልካም ልደት ይሁንልህ/ሽ!
እንኳን ደስ አለህ/ሽ/አላችሁ!
እንኳን ደስ አለህ/ሽ! አዲሱ መጽሓፍህ/ሽ ድንቅ ነው!
ከክፍሉ የፈተና ውጤትህ/ሽ እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ እንኳን ደስ አለህ/ሽ ማለት እፈልጋለሁ፡፡
እንኳን ደስ አለህ/ሽ! ደስ ብሎኛል፡፡ ውጤትህ/ሽ እጅግ በጣም ከፍትኛ ነው!
እጅግ ከፍትኛ ውጤት ስላመጣህ/ሽ እንኳን ደስ አለህ/ሽ ልበልህ/ሽ፡፡
መልካም ምኞት!
መልካም ዕድል!
መልካም ዕድል ለአንተ/ ለአንቺ/ ለእናንተ!
መልካም ዕድል ለአዲሱ ፕሮጀክትህ/ሽ!
መልካሙን ሁሉ እመኝልሀለሁ/ሻለሁ!
መልካሙን ሁሉ በህይወትህ/ሽ እመኝልሀለሁ/ሻለሁ!
መስማማት ፣ መቀበል
አዎ፡፡
እሺ/ መልካም፡፡
በእርግጥ/ በትክክል፡፡
በእርግጥ፡፡
ችግር የለም፡፡
በደስታ፡፡
ግሩም ሀሳብ ነው፡፡
ትክክል ነው፡፡/ እውነት ነው፡፡
እስማማለሁ፡፡
ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡
አለመስማማት
አይደለም፡፡
በፍፁም አይደለም፡፡
አይመስለኝም፡፡
መጥፎ ሀሳብ አይደለም፣ ግን በሌላ ጊዜ ብናየው፡፡
ይህ በፍፁም ትክክል አይደለም፡፡
እርዳታ መጠየቅ
ይቅርታ፣ ልትረዳኝ/ጂኝ ትችላለህ/ያለሽ?
ይቅርታ፣ ትንሽ እርዳታ እፈልጋለሁ፡፡
እባክህን/ሽን፤ ልትረዳኝ/ጂኝ ትችላለህ/ያለሽ?
ትንሽ ውለታ ልትሠራልኝ ትችላልህ?/ያለሽ?
መርዳት
ልርዳህ/ሽ?
እርዳታ ትፈልጋለህ/ትፈልጊያለሽ?
የምትፈልገው/ጊው እርዳታ አለ?
ልረዳህ/ሽ የምችለው ነገር አለ?
እንዴት ልርዳህ/ሽ?
ምስጋና ማቅረብ
አመሰግናለሁ፡፡
በጣም አመሰግናለሁ፡፡
ለእርዳታህ/ሽ አመሰግናለሁ፡፡
በእውነት አደንቃለሁ፡፡
በእውነት ለእርዳታህ/ሽ አመሰግናለሁ፡፡
በጣም ነው የረዳኻኝ/ሽኝ፡፡
የምስጋና ምላሽ
ምንም አይደል፡፡
በማንኛውም ሰዓት፡፡
ይሁን፡፡
ይሁን፣ እሺ፡፡
ይቅርታ መጠየቅ
በጣም አዝናለሁ፡፡
ይቅርታ አድርግልኝ፡፡
ይቅርታ አረፈድኩ፡፡
ይቅርታ፡፡ እንደዚያ ማለቴ አልነበረም፡፡
እባክህ/ሽ፣ ይቅር በለኝ/በይኝ፡፡
እባክህ፣ መጽሓፍህን/ሽን ስለ ጣልኩብህ/ብሽ ይቅርታ አድርግልኝ/ጊልኝ፡፡
የይቅርታ መልስ
እሺ ይሁን፡፡
አትጨነቅ/ቂ፡፡
አታስብ፡፡
ችግር የለውም፡፡
ትኩረት መሣብ
ይቅርታ!
ይቅርታ፣ ይህ የፒያሳ መንገድ ነው?
ይቅርታ ጌታዬ! ልትረዳኝ ትችላለህ?
ይቅርታ እመቤቴ! በጣም ቅርብ ፖስታ ቤት የቱጋ ነው?
ይቅርታ እህቴ! ሰዓት ስንት ነው?
ከጧት ሁለት ሰዓት!
ድገምልኝ ማለት
ይቅርታ?
ምን አልከኝ/ሽኝ?
ምን እንዳልክ/ሽ አልሰማሁም፡፡
እባክህ/ሽ፣ ልትደግምልኝ/ሚልኝ ትችላለህ/ያለሽ?
እባክህ/ሽ፣ የተናገርከውን ልትደግምልኝ/ሚልኝ ትችላለህ/ያልሽ?
ማብራሪያ መጠየቅ
አልገባኝም፡፡፡
እባክህ/ሽ፣ ታብራራልኛለህ/ ታብራሪልኛለሽ?
የቃሉ ትርጉም ምን ማለት ነው?
እንግሊዘኛዬ ጥሩ አይደለም፡፡
እባክህ/ሽ፣ አሁን የተናገርከውን/ሺውን ልታስርዳኝ/ጂኝ ትችላልህ/ያለሽ?
መረዳትን መግለጽ
ገባኝ/ ገብቶኛል ፡፡
ገብቶኛል/ ተረድቻለሁ፡፡
ገባኝ፡፡
ምን ማለትህ/ሽ ነው?
ግልጽ ነው፡፡
አልተርዳሁትም ለማለት
አላውቅም፡፡
አላልኩም፡፡
እኔ እንጃ፡፡/ አላውቅም፡፡
ባውቀው ደስ ይለኛል፡፡
ጥያቄ ማቅረብ
እባክህ/ሽ፤ ልትረዳኝ/ጂኝ ትችላለህ/ያለሽ?
እባክህ/ሽ፣ ቀስ ብለህ/ለሽ መናገር ትችላለህ/ያለሽ?
ተረጋግተህ ልታውራ/ሪ ትችላለህ/ያለሽ ?
እስከ አርብ አምሳ ብር ታበድረኛለህ/ሪኛለሽ?
እስክሪብቶህን/ሽን ለጥቂት ጊዜ ታውሰኛለህ/ሺኛለሽ? እሺ፡፡ ይሄው፡፡
ፈቃድ መጠየቅ
ልግባ? አዎ፣ ትችላለህ/ያለሽ፡፡
እባክህ/ሽ፣ ስልኬን ልጠቀም?
መጽሓፍክን/ሽን ብዋስ ቅር ይልሀል/ሻል?
እንዲፈጥን መጠየቅ
እባክህ/ሽ፣ ትንሽ ፈጠን አርገህ ትሠራው/ሪው?
እባክህ/ሽ፣ ፍጠን/ኝ ያለዚያ እንዘገያለን፡፡
ፍጠን/ኚ!
ና/ነዪ፣ እንሂድ!
ና/ነዪ፡፡
ትንሽ መፍጠን ትችላለህ/ያለሽ?
ማቆምን መጠየቅ
እባክህ/ሽ፣ አትጩህ/ሂ፡፡ (አታውራ/ሪ፣ አታልቅስ/ሽ፣ ወዘተ.)
እባክህ/ሽ፣ አቁመው/ሚው፡፡
እባክህ/ሽ፣ ለደቂቃ ታቆመው/ሚው ?
ጠብቅ/ቂ /አንድ ጊዜ ጠብቅ/ቂ፡፡
ጠብቅ/ቂ፡፡
በቂ ነው፡፡
የማትፈልገውን ነገር ለማስቆም መጠየቅ
አሁኑኑ አቁም/ሚ!
ይበቃል!
አትነዝንዘኝ/ዢኝ!/ አታስቸግረኝ/ሪኝ!
ይኸው ነው!
ማስጠንቀቂያ
ተጠንቀቅ/ቂ!
አውቶብሱን ተጠንቀቅ/ቂ!
እያየህ/ሽ ተራመድ/ጂ፡፡
ደረጃውን እያየህ/ሽ፡፡
ንግግርህን/ሽን አርም/ሚ፡፡ / አፍክን ጠብቅ/ቂ፡፡ / አንደበትክን/ሽን ቆጥብ/ቢ፡፡
ተጠንቀቅ/ቂ፡፡
ምክር መለገስ
ይሄን መፅሃፍ ማንበብ አለብህ/ሽ፡፡
በሀኪም መታየት አለብህ/ሽ፡፡
ለተወሰነ ቀን እረፍት ማድረግ አለብህ/ሽ፡፡
አንተን/ቺን ቢያደርገኝ፣ ኢትዮጵያ እሄድ ነበር፡፡
አድናቆትን መግለፅ
በጣም አምሮብሃል/ሻል፡፡ በጣም አምረሃል/ሻል፡፡
ሙሉ ልብሱ በጣም ያምራል!
አዲሱን የፀጉር አሠራርክን/ሽን ወድጄዋለሁ፡፡
ምርጥ ቤት አለህ/ሽ፡፡
እንግሊዘኛ በደንብ ትናገራለህ/ርያለሽ፡፡
አመሰግናለሁ፣ ደግ ነህ/ሽ፡፡
ግብዣ
ለልደቴ ልጋብዝህ/ሽ እፈልጋለሁ፡፡
ለሰርጌ ልጋብዝህ/ሽ እፈልጋለሁ፡፡
ለምን ወደ ሙዚቃው ትርኢት አንሄድም?
ግብዣን መቀበል
ለግብዣህ/ሽ አመሰግናለሁ፡፡
አመሰግናለሁ፡፡ በደስታ፡፡
ያን በጣም እወዳለሁ፡፡
ከደስታ ጋር፡፡
ምርጥ ሀሳብ ነው፡፡
ግብዣን አለመቀበል
ለግብዣው አመሰግናለሁ፣ ግን አልችልም፡፡
አልችልም፡፡ ጥናት አለብኝ፡፡
ይቅርታ፡፡ እኔ ዛሬ ማታ(ነገ/ቅዳሜ) ስራ አለብኝ፡፡
ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን ሥራ አለብኝ፡፡
መምጣት እፈልጋለሁ ግን አልችልም፡፡