Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Dime translations by topic.
ሻጭ፡- ምን ይፈልጋሉ?
ደንበኛ፡- ጫማ ፈልጌ ነበር፡፡
ሻጭ፡- ስንት ቁጥር ይፈልጋሉ?
ደንበኛ፡- ጥቁር 43 ቁጥር እፈልጋለሁ፡፡
ሻጭ፡- ይሄ፣ ጥራት ያለው 43 ቁጥር ጫማ ነው፡፡
ደንበኛ፡- መልካም፣ ዋጋው ስንት ነው?
ሻጭ፡- አንድ ሺ ብር ብቻ?
ደንበኛ፡- ኦ! በጣም ውድ ነው፡፡
ሻጭ፡- አይ፣ ርካሽ ነው፡፡
ደንበኛ፡- እሺ፣ አምስት መቶ ብር ትሸጥልኛለህ?
ሻጭ፡- አያዋጣም፡፡
ደንበኛ፡- እሺ፣ የመጨረሻው ዋጋ ስንት ነው?
ሻጭ፡- የመጨረሻው ዋጋ 800 ብር ብቻ ነው፡፡
ደንበኛ፡- እሺ፣ ይኸው፡፡
ሻጭ፡- እሺ፣ አምጣ፡፡
ደንበኛ፡- ይኸው፣ ውሰድ፡፡
ሻጭ፡- በጣም አመሰግናለሁ፣ ይልመድብህ፡፡
ደንበኛ፡- እሺ፣ እመጣለሁ፡፡