Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Kunama translations by topic.
የእኔ ስም / ስሜ እያሱ ነው፡፡
ስሜ ህይወት ነው፡፡/ ህይወት እባላለሁ፡፡
እድሜዬ ሃያ-አምስት ዓመት ነው፡፡
እኔ የተወለድኩት ግንቦት 3፣ 1984 ነው፡፡
የተወለድኩት በሆሣዕና ከተማ አጠገብ በአንዲት ትንሽ መንደር ውስጥ ነው ፡፡
ያደግኩት ሆሣዕና ከተማ ነው፡፡
የተማርኩት ሆሣዕና ነው፡፡
ከአምስት ዓመት በፊት ቤተሰቦቼ ወደ አዲስ አበባ ሄዱ፡፡
አባቴ ገበሬ ነጋዴ/ ሾፌር/ ኪም/አስተማሪ ነው፡፡
እናቴ ነርስ/ጋዜጠኛ/ልብስ ሰፊ/ጸሐፊ/መሀንዲስ ነች፡፡
ታናሽ ወንድም አለኝ፡፡ ስሙም ኢያሱ ነው፡፡
ወንድም አለኝ፣ ስሙም ይልማ ይባላል፡፡
የሁለት ዓመት ታላቄ ነው፡፡
ታናሽ እህቴ ሰላም ትባላለች፡፡ እሷም ተማሪ ናት፡፡
አላገባሁም፡፡
አግብቻለሁ፡፡ ቤተሰብም አለኝ፡፡
ሁለት ልጆች አሉኝ፣ እንድ ወንድ እና አንድ ሴት፡፡
የአሥራ አምስት እና የዘጠኝ ዓመት ሁለት ወንድ ልጆች አሉኝ።
ሴት ልጄ ሁለት ዓመቷ ነው፡፡
እኛ የምንኖረው በጋራ መኖሪያ ቤት ነው፡፡
እኛ የምንኖረው ትልቅ መናፈሻ አተገብ ነው፡፡
አድራሻዬ ፒያሳ ነው::
እኔ ከጓደኞቼ ጋር ማንበብ እና የእግር ጉዞ እወዳለሁ፡፡
እኔ የቅርጫት ኳስ እና የድሮ ፊልሞችን እወዳለሁ::
በትርፍ ጊዜዬ ፎቶግራፍ አነሳለሁ፡፡
በትርፍ ጊዜዬ ወፎችን ፎቶግራፍ አነሳለሁ፡፡
ባለቤቴ መጓዝ ትወዳለች፡፡
እሷ የተለያዩ አገሮችን ሳንቲሞች መሰብሰብ ትወዳለች፡፡
ባለቤቴ ምግብ መሥራት ይወዳል፡፡
በሙዚቃ መሳሪያዎች የተቀነባበሩ ዘፈኖችን መስማት አንወዳለን፡፡
ምን ትሠራለህ?/ ትሠሪያለሽ?/ ትሠራላችሁ?
ምን አይነት ሥራ ትሰራለህ? ትሰሪያለሽ? ትሰራላችሁ?
እኔ መሃንዲስ ነኝ፡፡
እኔ የሽያጭ ሥራ አስኪያጅ ነኝ፡፡
እኔ የቢሮ ጸሐፊ ነኝ፡፡
እኔ የቤተ-መጻሕፍት ባለሙያ ነኝ፡፡
እኔ የምሠራው ባንክ ቤት ነው፡፡ አንተስ/አንቺስ/ እናንተስ?
እኔ የምሠራው በሸቀጣሸቀጥ መደብር ነው፡፡
እኔ የምሠራው በምግብ ቤት ነው፡፡
ሥራዬ ማስተማር ነው፡፡
እኔ የምሠራው ጋዜጣ ላይ ነው፡፡
እኔ የምሠራው ኮምፒውተር ላይ ነው፡፡
እኔ የምሠራው ማስታወቂያ ላይ ነው፡፡
እኔ የምሠራው ቤቶች ግንባታ ላይ ነው፡፡
ትማራለህ?/ትማሪያለሽ? ወይስ ትሰራለህ?/ተሰሪያለሽ?
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ማህበረሰብ ትምህርት ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡