Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Oyda translations by topic.
እባክህን/ሽ፣ ወደ ቶክዮ የበረራ ትኬት መቁረጥ እፈልጋለሁ፡፡
በየትኛው አየር መንገድ መቁረጥ ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?
ቅናሹ የትኛው ነው?
መቼ መብረር ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?
በሚቀጥለው ሳምንት፡፡
ደርሶ መልስ ትኬት ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?
በረራው ምን ያህል ሰዓት ይወስዳል?
11 ሰዓት ይፈጃል፡፡
በዚህ ብሄድ ይሻላል፡፡
ስንት ትኬት ትፈልጋልህ/ጊያለሽ?
ለአትክልት ተመጋቢ የሚሆን ምግብ ማግኘት እችላለሁ?
ይችላሉ፡፡
በትኬት ማረጋገጫ ቦታ
ደህና አደርክ/ሽ:: ትኬትህ/ሽን ሊያሳዩኝ ይችላሉ?
ይኸው፡፡ ይህን ሻንጣ በእጄ መያዝ እችላለሁ?
አዎ፣ ይችላሉ፡፡
ማጨስ በሚፈቀድበት መተላለፊያ በኩል ወንበር ማግኘት እችላለሁ?
አዝናለሁ ወዳጄ፣ ይህ ማጨስ የማይፈቀድበት በረራ ነው::
የመተላለፊያ ወንበር ግን መያዝ ትችላለህ/ያለሽ፡፡
አመሰግናለሁ፡፡
ፓስፖርት በሚታይብተ ቦታ
ፖስፖርትህን/ሽን ማየት እችላለሁ?
ይኸው እንካ፡፡
የጉብኝትህ አላማ ምንድን ነው?
ለንግድ ሥራ ነው፡፡
ምን ያህል ጊዜ ትቆያለህ?
አስራ አምስት ቀን፡፡
በጣም አመሰግናለሁ፡፡ መልካም ቆይታ፡፡
ጉምሩክ ላይ
ማስመዝገብ የሚፈልጉት ነገር አለ?
ትንሽ ወይን ጠጅ እና ሲጋራ
ምን ያህል ወይን ጠጅ አለህ?
አራት ጠርሙስ
መልካም፣ ስንት ሲጋራ አለህ?
አስር ፓኮ ነው፡፡