Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Soddo translations by topic.
ደንበኛ፡- አልጋ አላችሁ?
እንግዳ ተቀባይ፡- አዎ፣ አለን፡፡
ደንበኛ፡- ለሁለት ቀን አልጋ ፈልጋለሁ?
እንግዳ ተቀባይ፡- እሺ፣ መልካም፡፡
ደንበኛ፡- ባለአንድ አልጋ ስንት ነው?
እንግዳ ተቀባይ፡- በቀን ሁለት መቶ ብር፡፡
ደንበኛ፡- ባለሁለት አልጋ ስንት ነው?
እንግዳ ተቀባይ፡- በቀን አራት መቶ ብር፡፡
ደንበኛ፡- ከገላ መታጠቢያ ጋር ነው?
እንግዳ ተቀባይ፡- አዎ፣ ከገላ መታጠቢያ ጋር ነው፡፡
ደንበኛ፡- ምን ያህል ሰፊ ነው?
እንግዳ ተቀባይ፡- አስር በአስር ነው፡፡
ደንበኛ፡- ቴሌቭዥን አለው?
እንግዳ ተቀባይ፡- አዎ፣ አለው፡፡
ደንበኛ፡- ምግብ ቤት አላችሁ?
ደንበኛ፡- የሌላ ሀገር ምግብ አገኛለሁ?
እንግዳ ተቀባይ፡- አዎ፣ ታገኛለህ፡፡
ደንበኛ፡- የመዋኛ ገንዳ አላችሁ?
እንግዳ ተቀባይ፡- አዎን፣ አለን፡፡
ደንበኛ፡- አሳንስር አለው?
እንግዳ ተቀባይ፡- አዎ፣ አለ፡፡
ደንበኛ፡- የመልቀቂያ ሰዓት ስንት ነው?
እንግዳ ተቀባይ፡- እስከ ስድስት ሰዓት፡፡
ደንበኛ፡- ልለቅ እፈልጋለሁ፤ ስንት አለብኝ?
እንግዳ ተቀባይ፡- እሺ፣ ሶስት መቶ አለብዎ፡፡