Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Tsamai translations by topic.
ሻጭ፡- ጤና ይስጥልኝ፣ ምን ይፈልጋሉ?
ደንበኛ፡- ስልክ መግዛት ፈልጌ ነበር፡፡
ሻጭ፡- ምን ዓይነት ስልክ ይፈልጋሉ?
ደንበኛ፡- የምፈልገው ሶኒ ኤሪክሰን ነው፡፡
ሻጭ፡- እሺ፣ ይኸው፡፡
ደንበኛ፡- ጥቁሩንና ቀዩን ማየት እችላለሁ?
ሻጭ፡- አዎ፤ ይኸው፡፡
ደንበኛ፡- ስንት ነው?
ሻጭ፡- በፊት 18000 ብር ነበር፣ አሁን ግን 12000 ብር ነው፡፡
ደንበኛ፡- እሺ! በጣም ጥሩ እገዛዋለሁ፡፡