Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Uduk translations by topic.
የት ነው የምትኖረው?
እኔ የምኖረው ፒያሳ ነው፡፡
ምን ያህል ትልቅ ነው?
መካከለኛ ነው፡፡
ሰፈርህ ምን ይመስላል?
ቆንጆ ነው፡፡
በሰፈርህ ምን ዓይነት ሰዎች ይኖራሉ?
አብዛኛዎቹ ነጋዴዎች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ተቀጣሪዎች ናቸው፡፡
የመንገዶች ሁኔታ ምን ይመስላል?
መንገዶቹ ጥሩ ናቸው፡፡
በሰፈርህ ብዙ ዛፎች አሉ?
አዎ፣ ብዙ ዛፎች አሉ፡፡
በሰፈርህ የመጫወቻ ስፍራ አለ?
አይ፣ የመጫወቻ ስፍራ የለም፡፡
በሰፈርህ ምን ያህል ሱቆች አሉ?
አስር ሱቆች አሉ፡፡
በሰፈርህ መናፈሻ ቦታ አለ?
አይ፣ መናፈሻ ቦታ የለም፡፡
በሰፈርህ የፍራፍሬና አታክልት መሸጫ አለ?
አዎ፣ የፍራፍሬና አታክልት መሸጫ አለ፡፡
በሰፈርህ የገበያ ማዕከል አለ?
አይ፣ የገበያ ማዕከል የለም፡፡
በሰፈርህ የቪዲዮ ማሳያ አለ?
አዎ ፣ የቪዲዮ ማሳያ አለ፡፡
በሰፈርህ መድኃኒት ቤት አለ?
አዎ ፣ መድኃኒት ቤት አለ፡፡
በሰፈርህ የስርቆት ችግር አለ?
አይ፣ የስርቆት ችግር የለም፡፡
በሰፈርህ ብዙ ጊዜ መብራት ይጠፋል?
አዎ፣ ብዙ ጊዜ መብራት ይጠፋል፡፡
በሰፈርህ የቧንቧ ውኃ አለ?
አዎ ፣ የቧንቧ ውኃ አለ፡፡
ሰፈርህ ሰላም ነው?
አይ፣ ሰፈሬ ብዙም ሰላም አይደለም፡፡
በሰፈርህ ስንት ትምህርት ቤቶች አሉ?
አንድ ትምህርት ቤት ብቻ አለ፡፡
መናኻሪያው ከሰፈርህ ምን ያህል ይርቃል?
ለሰፈሬ በጣም ቅርብ ነው፡፡
ሰፈርክን ትወደዋለህ?
አዎ፣ እወደዋለሁ፡፡