Choose the language you know and the language you want to learn before opening this section.
Read Amharic phrases alongside Zayse translations by topic.
ሻጭ፡- ምን ይፈልጋሉ?
ደንበኛ፡- ሱሪ ፈልጌ ነበር፡፡
ሻጭ፡- ምን ዓይነት ቀለም ይፈልጋሉ?
ደንበኛ፡- ጥቁር፡፡
ሻጭ፡- ስንት ቁጥር ነው የሚለብሱት?
ደንበኛ፡-እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ልትለካኝ ትችላለህ?
ሻጭ፡- ቁጥርዎ 34 ነው፡፡ ይኸኛው ይሁንልዎ?
ደንበኛ፡- ከምንድን ነው የተሠራው?
ሻጭ፡- ከሱፍ፡፡
ደንበኛ፡-ከጥጥ የተሠራ ይኖርሃል?
ሻጭ፡- አዎ፣ አለኝ፡፡
ደንበኛ፡-ልለካው?
ሻጭ፡- ይለኩት፡፡
ደንበኛ፡- ትንሽ ረዘመብኝ፣ ከዚህ አጠር ያለ ይኖርሃል?
ሻጭ፡- ይኸኛው አጠር ይላል፡፡
ደንበኛ፡-እሺ ልውሰደው፡፡